Service Alerts Sign Up for Newsletter @dashbus Twitter Updates
የ2022 ዓ.ም በጀት አመት የትራንዚተት ልማት እቅድ እና አዲሱ የDASH ኔትወርክ
ከዚህ የመኸር ወቅት ጀምሮ DASH አሁን አዲሱ የDASH ኔትወርክ ተብሎ የሚጠራውን ዋና ዋና መስመሮችን እና በሁሉም የDASH ተሳፋሪዎች ላይ ተጽእኖ የሚፈጥሩ የአገልግሎቶች ለውጦችን የሚይዘውን የ Alexandria Transit Vision Plan, የመጀመሪያውን ዙር ትግበራ ይጀምራል፡፡ እንደ 2022 –2027 ዓ.ም የበጀት አመት የትራንዚት ልማት እቅደድ/Transit Development Plan (TDP) እና የበጀት አሰራሮች አንድ ክፍል DASH በታቀዱት የአገልግሎት ለውጦች ላይ የህዝብ ግብረ መልስ እየተቀበለ ነው፡፡ ይህ ድረገጽ ስለታቀዱት ለውጦች የተመለከቱ ዝርዝሮችን እንደሁም የህዝብ ተደራሽነትና እንዴት ግብረ መልስ ሊቀርብ እነደሚችል የተመለከቱ መረጃዎችን ያቀርባል፡፡
እባክዎ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃና ዝርዝሮች ይመልከቱ፣ ከቨርቹዋል የማህበረሰብ ስብሰባዎች መካከል በአንዱ ላይ ይሳተፉ እና/ወይም ግብረ መልስዎን በኢሜይል በ dashbus@alexandriava.gov ይስጡ፡፡
የህዝብ ግብረ መልስ መስጫ ቀነ ገደብ አርብ፣ ሚያዚያ 16, 2021 ዓ.ም ያበቃል፡፡
አዲሱ የDASH ኔትወርክ ምንድን ነው?
አዲሱ የDASH ኔትወርክ የAlexandria Transit Vision (ATV) እቅድ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በታህሳስ 2019 ዓ.ም የATC የቦርድ ስብሰባ የጸደቀውን የተቀነሰ፣ የወጪ ቆጣቢ የመጨረሻው የ2022 ዓ.ም የATV እቅድን ይወክላለ፡፡ በመጨረሻው የ2022 ዓ.ም የATV እቅድ ውስጥ የሚካተቱት ሙሉ ምክረ ሀሳቦችና የአገልግሎት ጭማሪዎች በ FY 2022 – FY 2027 Alexandria Transit Company TDP. ስር በተገለጸው መሰረት እያደገ በሚሄድ መልኩ በመጨረሻው የ2022 እና 2023 ዓ.ም የATV እቅድ ስር ይቀርባሉ፡፡
ስለ 2022 ዓ.ም በጀት አመት አዲሱ የDASH ኔትወርክ የተመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች:
አዲሱ የDASH ኔትወርክ የአሁን እና የወደፊት የትራንዚት የማሽከርከር ፍላጎትን እንዲያሟላ እና ብዙ ሰዎች በቀን ውስጥ ለሚያደርጓቸው ተጨማሪ ጉዞዎች ትራንዚት እንዲጠቀሙ ለማስቻል የታቀደውን የአሌክሳንደሪያ የአውቶቡስ ዲዛይንን ይወክላል፡፡